የቢሮ ኃላፊ መልዕክት

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ
አቶ ሙስጠፋ ኢሳ
በአገራችንና በክልላችን ጥራት ያለው እና ፈጣን ዕድገትን እንዲሁም ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ ኢኮኖሚ መገንባት ስራ አጥነትን የመቅረፍ ድርሻው ከፍ ያለ ነው፡፡ ቢሮው በተሰጠው ተልዕኮ መሠረት የስራ ዕድል ፈጠራ ምህዳርን በማስፋትና በክልሉ የሥራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ሥራ ፈላጊ ዜጎችን በመለየት፣ በማደራጀት፣ አዋጭነታቸው በተረጋገጡ ፓኬጆች ላይ ስልጠና እንዲዲደገኙ የማድረግ፣ የስራ እድል በመፍጠር ገቢያቸውን እንዲያሳደጉና የኑሮ ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ ማድረግ ነው፡፡
ድህነትን ደረጃ በደረጃ ለማስወገድ እና ስራ አጥነትን ትርጉም ባለው ደረጃ በመቀነስ የማክሮ ኢኮኖሚን ሚዛን ለማስጠበቅ በሚሰራው ስራ የዘርፉ ሚና የጎላ ነው፡፡ ለዜጎች የሥራ ዕድል የመፍጠርና የሥራ አጥነት ጉዳይ በየትኛውም ኢኮኖሚ ወሳኝ የፖሊሲ ማሻሻያዎች እየተደረገ የሚመራና ባለብዙ ትርጉም የፖለቲካ-ኢኮኖሚ ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም በሀገራችን ከለውጡ በኋላ በፌዴራል መንግሥት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ሰፊ የአሰራርና የአደረጃጀት ለውጥ ከተደረገባቸው ዘርፎችም አንዱ ሲሆን የሥራ አጥነትን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችሉ አዳዲስ የፖሊሲ፣ የአሰራርና የሪፎርም እሳቤዎችን በማውረድና ተግባራዊ በማድረግ ሰፋፊ ውጤቶችን ለማስመዝገብ አስቻይ አቅሞችን እየፈጠረ ይገኛል፡፡
ከዚህም በመነሳት የክልሉ የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ የ10 ዓመቱን የዕድገትና ትራንሰፎርሜሽን እቅድ መነሻ በማድረግ ያለፉትን አመታት አፈፃፀም ተገምግሟል፡፡ በግምገማውም ያልተሳኩ ግቦችን ጉድለት ለማሟላትና የነበሩ ጥንካሬዎችን በመጠቀም በስትራቴጅክ ዕቅድ ለማመላከት ተሞክሯል፡፡
ሴክተሩ ዘላቂና አስተማማኝ የስራ ዕድል መፍጠር፣ ጠንካራ ተቋም መገንባትና ተወዳዳሪና የውጭ ምርት ተኪ አምራች ኢንተርፕራይዞችን መፍጠር የሴክተሩ ስትራቴጂክ ትኩረት መስክ አድርጎ ነእየተሰራ ነው፡፡ በዚህም በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ፣ በገጠርና በከተማ ስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፎች ተደራጅቶ በሶስቱ የዕድገት ተኮር የስራ ዘርፎች ተጨባጭ ስራ ዕድል ለመፍጠር እየተሰራ ነው፡፡
የዜጎችን ስራ ክህሎትና የስራ ፈጣሪነት አመለካከት በማጎልበት፣ የስራ ባህል በማሻሻል፣ የግብአት ማነቆዎችን በመፍታት ከዩንቨርስቲዎች፣ ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት፣ ከምርምር ተቋማት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ጠንካራ ቅንጅት በመፍጠር ወጣቶችን፣ ሴቶችን፣ ምሩቃንን፣ ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ መትጋት ይገባል፡፡ተጨማሪ ያንብቡ
ወልቂጤ , ኢትዮጵያ
011 365 9189