የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማስተባበሪያ ዩኒት
ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ ሥራ የመፍጠር፣ በአንድ ማዕከል ምቹ የስራ አካባቢ የመፍጠር፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ማስተዳደር፣ በከተማ ሥራ እድል ፈጠራ ዘርፍ ሥር ባሉ ዳይሬክቶሬቶች የሚሰጡ አገልግሎቶች ፈጣን፣ ተደራሽ እና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ በአንድ ማዕከል እንዲሰጥ ማድረግ፣ የህዝብ ቁጥርን መሠረት ባደረገ መልኩ አዳዲስ የአንድ ማዕከል አገልግሎትሎት መስጫ ጣቢያዎች እንዲከፈቱ በማድረግ ለህዝብ ተደራሽነቱን ማረጋገጥ፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ግንባታ ወጥነት እንዲኖረው ዲዛይን እንዲዘጋጅ ማድረግ፣ ዲዛይኑን ማሰራጨትና አፈጻጸሙን መከታተል፣ በየማዕከሉ ያሉ የማቴሪያልና ሎጀስቲክ ክፍተቶችን በጥናት በመለየት ሀብት በማፈላለግ ለአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎቹ ቁሳቁስ እንዲሟላ ማድረግ፣ የመረጃ ማሰባሰብ፣ ማደራጀት፣ የመተንተንና የማሰራጨት ሥራዎችን የሚሰራ ነው፡፡
ወልቂጤ , ኢትዮጵያ
011 365 9189