የመሰረተ ልማትና ክላስተር ማዕከላት ዳይሬክቶሬት
የመሰረተ ልማትና ክለስተርማዕከላት ዳይሬክቶሬት ማለት የአሰራር ስርአት ክፍተት፣ የምርት ማሳያና የመሸጫ ህንጻ አቅርቦት ጥያቄ፣ የጨረታ መርሀ-ግብር መረጃ ፍላጎት፣ የጨረታ የአሰራር ህግ ተከባሪነት ጥያቄ፣ የኢንዱስትሪ ደህንነትና ልማት በግብዓትነት በመቀበል የማንፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ፖቴንሻል ጥናት በማካሄድ፣ የማምረቻና መሸጫ ማዕከላት ግንባታ ዲዛይን እንዲዘጋጅ በማድረግ፣ ሲጸድቅም የግንባታ ጨረታ መርሃ-ግብር ማዘጋጀትና ለህዝብ መረጃ በመስጠት፣ የጨረታ አሸናፊዎችን መለየትና ውል በማስገባት፣ የግንባታ ድጋፍ ስራ በመስራት፣ የተገነቡ የምርት ማሳያና መሸጫ ህንጻዎችን በመረከብና በማስተላለፍ፣ ለማምረቻና መሸጫ ህንጻዎች ግንባታ አገልግሎት የሚውል ቦታ በማልማት፣ የማዕከላቱን መሰረተ ልማት በማደስና በማስፋፋት፣ የለሙ ማምረቻ ማዕከላትን ለምርታማነት ምቹ እንዲሆኑ በማድረግ፣ በአካባቢ ደህንነት ዙርያ የስልጠናና ምክር በመስጠት፣ ነባር የምርት ማሳያና መሸጫ ህንጻዎችን የማስፋፋትና በማጠናከርና በማስተዳደር ለኑሮና ለልማት ምቹ የሆነ አካባቢ እንዲኖር በማድረግና በተገነቡ ክላስተሮች፣ የምርት ማሳያና የመሸጫ ማዕከላት ተጠቃሚ የሆኑ አነስተኛ፣ መካከለኛና ከፍተኛ ኢንተርፕራይዞችን መፍጠር ነው፡፡
ወልቂጤ , ኢትዮጵያ
011 365 9189