ስለ ቢሮው
የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ በሀገራችን ከለውጡ በኋላ በፌዴራል መንግሥት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ሰፊ የአሰራርና የአደረጃጀት ለውጥ ከተደረገባቸው ዘርፎችም አንዱ ሲሆን በአዋጅ ቁጥር 1263/2014 ኃላፊነትና ሥልጣን የተሰጠው የፌዴራል ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሥራ፣ ሥራ ሥምሪትና ገበያ ዘርፍ የተቀመጡ ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮችን መነሻ በማድረግ በሀገሪቱ የሥራ አጥነትን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችሉ አዳዲስ የፖሊሲ፣ የአሰራርና የሪፎርም እሳቤዎችን በማውረድና ተግባራዊ በማድረግ ሰፋፊ ውጤቶችን ለማስመዝገብ አስቻይ አቅሞችን እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ክልላችንም በአዲስ መልክ ከተደራጀ በኋላ የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በአዋጅ 199/2015 ከተቋቋሙ አስፈጻሚ መ/ቤቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ ቢሮውም በስሩ በሶስት ዋና ዋና ዘርፎች ማለትም የገጠር ስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ፣ የከተማ ስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ እና የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ልማት ዘርፍ እንዲሁም በደጋፊ የስራ ክፍሎች ተደራጅቶ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ክላስተር ከሚገኙ ቢሮዎች አንዱ ነው፡፡
ወልቂጤ , ኢትዮጵያ
011 365 9189