የቢሮው ሥልጣንና ተግባር
የሥራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ
የክልሉ ሥራ ፈላጊዎች በተለይም ወጣቶች እና ሴቶች በስራ ፈጠራ ላይ በስፋት እንዲሰማሩ ግንዛቤ ይፈጥራል፣ የስልጠና ድጋፍ፣ የመስሪያ ቦታ፣ ብድር፣ ገበያ ትስስር ምክር እና ሌሎች ድጋፎች እንዲያገኙ ያደርጋል፣ ያመቻቻል፤
ኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪ ሆነው ቀጣይነት ላለው ልማትና ለኢንዱስትሪ ልማት ጽኑ መሠረትን መጣል እንዲችሉ ድጋፍ የሚሰጡ ተቋማትን ያጠናክራል፣ ያደራጃል፤
የኢንተርፕራይዞች የድጋፍ ፓኬጅ ያዘጋጃል፡ ያቀናጃል፡ ያስፈጽማል በስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፤
ለኢንተርፕራይዞች የስልጠና፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የብድር፣ የማሽን፣ የገበያ ትስስር እና የተሟላ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡
የስራ ፈጠራ እና የስራ እድል ላይ ጥናት ያደርጋል፣ ለሚመለከተው አካል በማቅረብ ሲጸድቅ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣
ኢንተርኘራይዞች ላይ ያሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን በጥናት ለይቶ በማቀናጀት እዲስፋፉ ያደርጋል፤ ተመሳሳይነት ያላቸውን ትስስር እንዲኖር ይሰራል፤
ለኢንተርፕራይዝ ልማት የሚውሉ የክልሉ የተፈጥሮ ሀብት ላይ ከሚመለከተው አካል ጋር ጥናት ያካሄዳል፡ የጥናቱ ውጤት ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፡ ሲጸድቅ በስራ ላይ ያውላል፤
የአንድ ማዕከላትን አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ይዘረጋል፣ ያደራጃል፣ ያጠናክራል፣
ኢንተርፕራይዞች የሚመዘገቡበትን፡ የሚደራጅበትን፡ ህጋዊ ሰውነት የሚያገኙበትን አሰራር ከሚመለከተው አካል ጋር ይሰራል፣
ኢንተርፕራይዞች የሂሳብ አያያዝ ምክር እና የኦዲት አገልግሎት እንዲያገኙ ድጋፍ ያደርጋል፣ ሂሳባቸውን ይመረምራል፡ እንዲመረመር ያደርጋል፡ በአፈጻጸማቸው እና ሀብት አያያዛቸው ላይ የኢንስፔክሽን ስራ ያካሄዳል፣ የእርምት እርምጃ ይወስዳል፡
የስራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት በሁሉም ደረጃ እንዲቋቋም ያደርጋል፣ የምክር ቤቱን ስራ ያደራጃል፡ አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል፤
ከጥቃቅን ወደ አነስተኛ ኢንተርኘራይዝ የእድገት ደረጃቸውን በመጠበቅ ከጀማሪነት ወደ ታዳጊ ወደ መካከለኛና ከፍተኛ እንዲሸጋገሩ ያደርጋል፣ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፤ መረጃቸውን በመለየት ይይዛል፣ ደረጃውን የጠበቀ ድጋፍ ይሰጣል፡
በየደረጃው ድጋፍ አግኝተው ከመካከለኛ ወደ ከፍተኛ አምራች ኢንተርፕራይዝነት የተሸጋገሩትን አምራች ኢንዱስትሪ ወደ ሚያስተባብር ተቋም ከነሙሉ መረጃቸው ያስተላልፋል ፡፡
ለሚያደራጃቸውና ለሚደግፋቸው ኢንተርፕራይዞች የማምረቻ፣ የምርት ማሳያና መሸጫ፣ የገቢያ ማእከላትና ሼዶችን ይገነባል፣ ያስገነባል፣ ይደግፋል፣ ለኢንተርፕራይዞች ያስተላልፋል፣ የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፣ ያስተዳድራል
የኢንተርፕራይዞችን ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ይዘረጋል፣ ያስተዳድራል
የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ዘርፍ ማህበራትን እንዲያደራጁና እንዲያጠናክሩ ድጋፍ ያደርጋል፤
ሞዴል ኢንተርፕራይዞች ዕቅድ አሰጣጥ ሥርዓት ይዘረጋል ፣ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፤
የኢንተርኘራይዝ ልማት ተደራሽነት እና ምርታማነት ለማጠናከር ከሚመለከተው አካል ጋር ይሰራል፣ መካከለኛ ስልጠና ያለው የሰው ኃይል እንዲያገኙ ያመቻቻል፣ በክልሉ ገጠር አካባቢዎች የሚስተዋለውን ሥራ አጥነት መሠረት በማድረግ የሥራ ዕድል ለመፍጠርና ዘላቂ ልማት ለማምጣት የሚያስችል ስልት ይቀይሳል፣ አፈፃፀሙን ይገመግማል፣ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ያቀርባል፤
የኢንተርፕራይዝ ልማት ተደራሽነት እና ምርታማነት ለማጠናከር ከሚመለከተው አካል ጋር ይሰራል፣ መካከለኛ ስልጠና ያለው የሰው ኃይል እንዲያገኙ ያመቻቻል፣
በክልሉ ገጠር አካባቢዎች የሚስተዋለውን ሥራ አጥነት መሠረት በማድረግ የሥራ ዕድል ለመፍጠርና ዘላቂ ልማት ለማምጣት የሚያስችል ስልት ይቀይሳል፣ የአፈፃፀም አቅጣዎችን የስቀምጣል፣ ይከታተላል፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ይሰራል፤
የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና ልማት ስራዎችን ለማፋጠን የሚረዱ ስትራቴጂዎችን ይነድፋል፣ መርሀ-ግብሮችን ያዘጋጃል፣ ሲፈቀድም አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ከሚመለከተው የባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ይሰራል
የከተማ ምግብ ዋስትና ፕሮግራምን በባለቤትነት ያስተባብራል፣ ከሚመለከታቸውም አካላት ጋር በመቀናጀት ይደግፋል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣ ዘላቂነት ካለው የልማት ተግባር ጋርም ያስተሳስራል፣
ዓላማውን ለማስፈጸም የሚችሉ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፣
ወልቂጤ , ኢትዮጵያ
011 365 9189