Skip to main content

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በበጀት አመቱ አንደኛ ሩብ አመት በዕድገት ተኮር ዘርፎች ከ46ሺ በላይ ቋሚ የስራ ዕድል መፈጠሩ ተገለጸ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በበጀት አመቱ አንደኛ ሩብ አመት በዕድገት ተኮር ዘርፎች ከ46ሺ በላይ ቋሚ የስራ ዕድል መፈጠሩ ተገለጸ።

 (ወልቂጤ፣  ጥቅምት 08/2018 )፣ የክልሉ ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ የበጀት አመቱን አንደኛ ሩብ አመት የስራ አፈጻጸም በዱራሜ ከተማ ገምግሟል።

ቢሮው በኢትዮጵያ የስራ ገበያ መረጃ ስርዓት (ELMIS) ስልጠና በሚሰጥበት መድረክ ላይ ነው የስራ አፈጻጸሙን የገመገመው።በበጀት አመቱ አንደኛ ሩብ አመት በዕድገት ተኮር ዘርፎች ከ46ሺ 6መቶ በላይ ቋሚ የስራ ዕድል በክልሉ መፈጠሩ የተገለጸ ሲሆን የስራ ዕድል የተፈጠረባቸው ዘርፎች በግብርና ኢንዱስትሪ እና አገልግሎት እንደሆነ በመድረኩ ተመላክቷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ መድረኩን ሲያጠቃልሉ እንዳሉት በየመዋቅሩ የሚታየውን የስራ ገበያ መረጃ ስርዓት (ELMIS) ምዝገባ አፈጻጸም ማቀራረብ ይገባል ብለዋል።አቶ ሙስጠፋ በሶስት ስትራቴጂክ የትኩረት መስኮች፤ በተቋም ግንባታ፣ ቋሚና አስተማማኝ የስራ እድል ፈጠራ እንዲሁም ተወዳዳሪ ኢንተርፕራይዞችን መፍጠር ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የቢሮዉ ምክትልና የከተማ ዘርፍ ስራ ዕድል ፈጠራ ኃላፊ  አቶ ታምራት ተስፋሁን በበኩላቸው በክልሉ 47 ባዮ ማትሪክ የለባቸው 172 የስራ ማዕከላት መኖራቸውን ገልጸው ሰልጣኞች ባገኙት ስልጠና የስራ ገበያ መረጃ ስርዓትን (ELMIS) ተግባራዊ ለማድረግ መትጋት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

Image