ዘላቂና አስተማማኝ ስራ ዕድል ለመፍጠርና ምርታማነትን ለማሳደግ ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማጠናከር እንደሚገባ የክልሉ የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ አስታወቀ
ዘላቂና አስተማማኝ ስራ ዕድል ለመፍጠርና ምርታማነትን ለማሳደግ ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማጠናከር እንደሚገባ የክልሉ የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ አስታወቀ
(ወልቂጤ ፦ታህሳስ 3/2018) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የ5 ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማና በቀጣይ አቅጠጫ ዙሪያ በወልቂጤ ከተማ እየመከረ ነው።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ እንደገለፁት ስራ አጥነትን ደረጃ በደረጃ ለመቀነስና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በክልሉ ያሉ ፀጋዎችን በመለየት ለህዝቡ ተጠቃሚነት በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው።ቢሮው ዘላቂና አስተማማኝ የስራ ዕድል ለዜጎች መፍጠር፣ የኢንተርፕራይዝ ልማትን ማስፋፋት እና በተቋማት ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ስለመሆኑም ተናግረዋል።ዘላቂና አስተማማኝ ስራ ዕድል ለመፍጠርና ምርታማነትን ለማሳደግ ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር የተጀመረውን ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ መትጋት እንደሚገባም ጠቁመዋል።
የተመረጡ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የ5 ወራት አፈጻጸም ሪፖር እያቀረቡ ሲሆን በቀጣይ በታዩ ጠንካራና ደከማ አፈጻጸሞች ዙሪይ ሰፊ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።በመድረኩም የክልል፣የዞንና ልዩ ወረዳዎች የሴክተሩ ዋናና ምክትል ኃላፊዎች ተገኝቷል
ወልቂጤ , ኢትዮጵያ
011 365 9189