Skip to main content

የምግብ ስረዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ለስራ ዕድል ፈጠራ የሚኖረው አበርክቶ ጉልህ በመሆኑ በፕሮግራሙ የሚገኙ እድሎችን አሟጦ መጠቀም እንደሚገባ ተጠቆመ

የምግብ ስረዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ለስራ ዕድል ፈጠራ የሚኖረው አበርክቶ ጉልህ በመሆኑ በፕሮግራሙ የሚገኙ እድሎችን አሟጦ መጠቀም እንደሚገባ ተጠቆመ

(ወልቂጤ፣ ታህሳስ 21/2018)፣ በክልሉ የምግብ ስረዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ከሚተገበርባቸው ወረዳዎችና ቀበሌያት ለተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎችና በቀበሌ ደረጃ ለሚገኙ ሞዴል ኢንተርፕራይዝ ሰብሳቢዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በቡታጅራ ከተማ እየተሰጠ ነው።ስልጠናውን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራ ዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ከክልሉ የምግብ ስረዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን በአነስተኛና ንግድ ስራ ኢንተርፕራይዝ አደረጃጀትና አመራር፣ በአግሪ ቢዝነስና ፋይናንሻል ማኔጅመንት ላይ ያተኮረ ነው።

የክልሉ ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ፣ የምግብ ስረዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ለስራ ዕድል ፈጠራ የሚኖረው አበርክቶ ጉልህ በመሆኑ በፕሮግራሙ የሚገኙ እድሎችን አሟጦ መጠቀም ይገባል ብለዋል።በፕሮግራሙ ድጋፍ ወደ ስራ የገቡ ኢንተርፕይዞች ለውጤታነት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባም አመላክተዋል።

ስልጠናው ለዘርፉ ውጤታመነት የሚኖረው ሚና ጉልህ ነው ያሉት የቢሮ ኃላፊው፣ በፕሮግራሙ የቀረበውን ዕድል በተገቢው መጠቀም ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።የምግብና ስረዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ከግበዓት አቅርቦት አኳያ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲያቀጥልም አቶ ሙስጠፋ ጠይቀዋል።የስራ አጥነትን ችግር ለመቅረፍ ቅንጅታዊ አሰራርን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባም ተናግረዋል።

በስልጠናው የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ የገጠር ስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ባለሙያዎች፣ የመዋቅር የስራ ኃላፊዎች፣ የወረዳ ፕሮጀክት አስተባባሪዎችና ፎካሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።

Image