Skip to main content

ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የሀገራችንን የኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ስብራቶችን በመቅረፍ ረገድ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን የክልሉ የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ገለፀ

ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የሀገራችንን የኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ስብራቶችን በመቅረፍ ረገድ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን የክልሉ የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ገለፀ

(ወልቂጤ ፦ ታህሳስ 22/2018) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ከታችኛው መዋቅሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር በማረቆ ልዩ ወረዳ ቆሼ ከተማ ምክክር እየተካሄደ ነውየቢሮው ምክትልና የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ዙልፋ አለዊ እንደገለፁት ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የሀገራችንን የኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ስብራቶችን በመቅረፍ ረገድ ያለው ሚና ከፍተኛ ነው።

ዘርፉ የቴክኖሎጂ እና የእውቀት ሽግግርን በማፋጠን ከውጭ በከፍተኛ ወጪ በዶላር የሚገባውን ምርት በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የሚያስችል እና ለዘላቂ የስራ ዕድል ፈጠራ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ከእለታዊ ምግብ ፍጆታ ባለፈ ሀገር የማበልፀግ ጉዳይ በመሆኑ የተሰጠንን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት እና የህዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ መትጋት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

የማረቆ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀማል አማሮ እንደተናገሩት የስራ ዕድል ፈጠራ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠሩ በሀገር ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል ለማየት ተችሏል።በመሆኑም በቀጣይ ከዘርፉ ሁሉም ህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንዲሆን በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለው በልዩ ወረዳው አሁን ያለውን ሰላም በዘላቂነት ለማስፈን ህብረተሰብ የለመደውን የሰላም እሴቶችን በማጎልበት ለሰላም ዘብ መቆም ያስፈልጋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በመድረኩም የቢሮ ምክትል ኃላፊዎች፣ የዞን፣ ልዩ ወረዳዎች የዘርፉ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

Image