የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ የ2018 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም በወልቂጤ ከተማ ተገመገመ ።
የሥራ ዕድል ፈጠራና እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ የክልሉን የስራ ዕድል ፈጠራ ስራዎች የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ገመገመ ።
ወልቂጤ፦ታህሳስ 24/2018
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ የ2018 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም በወልቂጤ ከተማ ተገመገመ ።
የግምገማ መድረኩን የመሩት አቶ ታምራት ተስፋሁን የቢሮው ምክትል ሀላፊ እና የከተማ ስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፈ ሃላፊ ሲሆኑ በመድረኩም ባለፉት ስድስት ወራት በክልሉ ስራ ዕድል ፈጠራ መሪነት የተከናወኑ አበይት ተግባራት በጥልቀት የተገመገሙ ሲሆን በተግባር አፈፃፀም ሂደት የተገኙ ስኬቶች እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በዝርዝር ተፈትሾዋል።
በተጨማሪም አዳዲስ ኢኒሸቲቮች የተመራበት አግባብ በክልሉ የተደረጉ የንቅናቄ ተግባራትና የህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተደረጉ ርብርቦችን እንዲሁም ሌሎች ነባራዊ ሁኔታዎችን ተፈትሾዋል።
በግምገማ መድረኩ የቢሮው የስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በዓመቱ ለ400 ሺ በግማሽ ዓመቱ የዕቅዳችንን 60% ለመፈጸም ግብ ጥለን የተመራ ሲሆን በዚህም ለ240,000 ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ 247,230 (ከ100% በላይ ነው) ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል፡፡ ሌሎች መንግስታዊ ድጋፍ ስራዎችም ውጤታማ መሆናቸውን ማየት ተችሏል፡፡
ለዕቅዶቻችንን ስኬት ከሚነሱ ጉዳዮች ውስጥ የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎች በተገቢ ሁኔታ መመራታቸው፣ አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን ከየአካባቢው ጸጋዎች ጋር በማቀናጀት መተግበራቸው፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ ስራዎች መሰራታቸው፣ ችግር ፈቺ የድጋፍና ክትትል ስራዎች መሰራታቸውና የዘርፉ ስራዎች በየሳምንቱ በርዕሰ መስተዳድሩ መገምገማቸው ናቸው፡
በአፈፃፀም ግምገማ መድረኩ የዘርፍ ኃላፊዎችና እና የማኔጅመት አባላት ተገኝተዋል።
ወልቂጤ , ኢትዮጵያ
011 365 9189